ቀን 02/12/2017 ዓ.ም
የምዝገባ ማስታወቂያ
በግል ትምህርት ቤት ተምራችሁ ምድባችሁ ወደዚህ ለሆነ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ
የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አንኳን ለ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሠላም አደረሳችሁ እያለ በግል ትምህርት ቤት ተምራችሁ ምድባችሁ ወደዚህ ለሆነ አዲስ ተማሪዎች ማለትም ባሸዋም ፣አስቴር ቤተፍቅር እና አስርአዋርያ ት/ቤቶች ከ05/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/12/2017 ዓ.ም ብቻ ምዝገባ የምናከናውን መሆኑን እያሳወቅን ለመመዝገብ ስትመጡ የሚያስፈልጉ ነገሮች
የማሪው/ዋ 1 3*4 ጉርድ ፎቶ 6 ወር ያልሞላው ፣ የልደት ሠርተፍኬት እና የፋይዳ መታወቂያ
የወላጅ 1 3*4 ጉርድ ፎቶ 6 ወር ያልሞላው እና የወላጅ መታወቂያ እና ፎቶ ኮፒ
ከተማረበት/ችበት ትምህርት ቤት ኦሪጅናል መሸኛ እና የተዘዋወረበት የትምህርት ማስረጃ ግዴታ ማሟላት ይጠበቅባችኋል
ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከምናሳውቃችሁ ድረስ የልደት ሠርተፍኬት እና የ ናሽናል ኤይዲ ፋይዳ አዘጋጅታችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ በትህትና እናሳውቃን፡፡
ት/ቤቱ ፡፡
.